(የካቲት 3/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ይዘት ማበልጸግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ባለሙያ የሆኑት አቶ ጸጋዮ አጋጨው በኮንፊሊክት ማኔጅመንት ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ በማቅረብ እውቀታቸውን ያካፈሉ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ የቀረበው ሰነድ ለስራ ውጤታማነት ብቻ ሳይሆን ለግል ህይወትም ከፍተኛ አበርክቶ ያለው መሆኑን በመግለጽ ሰራተኛው ወደ ራሱ በመውሰድ ወደተግባር መቀየር ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
0 Comments