የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(ጥር 26/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ ማኔጅመንት አባላትና የትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

       

በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደስታ አብርሃ ከመረጃ ጽንሰ ሀሳብና መረጃ ለትምህርት ስራዉ ያለዉን ፋይዳ መሰረት ያደረገ ሰነድ በማቅረብ እውቀታቸውን ያካፈሉ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በትምህርት ልማት ስራ ውጤታማነት ላይና የሚወሰኑ ውሳኔዎች በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ መረጃ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት በመግለጽ በተለይ የትምህርት መረጃን በማዘመን ጥራቱና ወቅታዊነቱ የተጠበቀ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር በትኩረት መሰራት እንደሚገባው አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

        

0 Comments