(ጥቅምት 6/2017 ዓ.ም) የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት በቢሮው ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችና 11ዱ ክፍለ ከተሞች ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ::
በኦረንቴሽኑ የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀምን የሪፎርም ሥራዎችን አስመልክቶ ሥራዎችን ለማከናወን የተሄደበትን ርቀት በመመልከት በተፈለገው ልክ መሆኑን በማረጋገጥ ቀጣይ የተሻለ ሥራ ለመስራት እንዲቻል አቅም እንደሚፈጥር ተገልፃል::
ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን የሰጡት የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ ኃላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የትምህርት ማህበረሰቡ ለሚያቀርባቸው የአገልግሎት ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠትና በመደበኛ ሥራ እቅድ አፈፃፀም ውጤታማ ለመሆን የሪፎርም ስራን ማጠናከር ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል:: አያይዘውም ክትትልና ድጋፉ በሩብ ዓመቱ ዳይሬክቶሬቶች እቅድን በአግባቡ አዘጋጅቶ ከማከናወን አንፃር ያሉበትን ደረጃ በማየት በተገቢ ስራቸውን ያከናወኑትን በመለየት እጥረት ያለባቸውን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚያስችል አብራርተዋል :: መዛኞችም ክትትልና ድጋፉ ለቀጣይ ምዕራፎች የሚታዩ ጉድለቶችን ለመሙላት መደላድል የሚፈጥር መሆኑን በመረዳት. በኃላፊነት ስሜት ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል ::
የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋአገኘሁ የክትትልና ድጋፍ ስራው ቀደም ሲል ይደረግ ከነበረው ጠንከር ባለ መልኩ በማካሄድ ለሪፎርም ስራው ስኬታማነትና በቀጣይ 6 ወር ለሚካሄድ ምዘና አቅም መሆን እንዲችል መዛኞች በትኩረት እንዲሰሩ ጠይቀዋል::
የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ለ1ኛ ሩብ ዓመት የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ::
0 Comments