(ጥር 28/2017 ዓ.ም) ከየትምህርት ቤቱ በመረጃ መሰብሰቢያ ቅጹ መሰረት ተሞልተው የተሰበሰቡ መረጃዎች የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ወዳበለጸገው stat edu2.2017 ሶፍትዌር በመጫን ላይ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ወልደኪዳን ገልጸው የቢሮውን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች የመረጃ መሰብሰቢያ ቅጾቹ በአግባቡ ተሞልተው ወደ ሶፍትዌር እንዲጫኑ እያደረጉ የሚገኙት ድጋፍና ክትትል ለስራው ውጤታማነት ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አመላክተዋል።
የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም በበኩላቸው መረጃዎቹ ቀደም ሲል ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በተላከ የመረጃ መሙያ ቅጽ መሰረት በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ተሞልተው ወደ ክፍለ ከተማ መላካቸውን ጠቁመው ወደ ሶፍትዌር የተጫኑ መረጃዎችን በማጥራት ለትምህርት ሚኒስቴር የመላክ ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
መረጃዎቹ በአይ ሲቲ መምህራን እና በክፍለ ከተማና ወረዳ የመረጃ ባለሙያዎች አማካይነት ወደሶፍትዌሩ በመግባት ላይ እንደሚገኙ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ አዲስ ዘገየ ገልጸዋል።
የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ወልደኪዳን ከቡድን መሪዎቹ አቶ ደስታ አብረሀም እና ከአቶ አዲስ ዘገየ ጋር በመሆን መረጃዎቹ ወደ ሶፍትዌሩ እየተጫኑ የሚገኙበትን ሂደት የተመለከቱ ሲሆን ምልከታው ከተደረገባቸው ተቋማት መካከል የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ታደሰ ፣እንዲሁም የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሌሊስቱ ተስፋዬ እና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የመረጃ ቡድን መሪ አቶ ተካልኝ ጌታቸው መረጃዎቹ በአይ ሲቲ መምህራን እና በመረጃ ባለሙያዎች አማካይነት ወደ ሶፍት ዌር እየገቡ መሆናቸውን ጠቅሰው ጽህፈት ቤቶቹም ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
0 Comments