ከኢስኩል ሲስተም ጋር በተገናኘ ለአይ ሲቲ መምህራን የሚሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና እንደቀጠለ ነው።

by | ዜና

(ጥር 24/2017 ዓ.ም) መርሀ ግብሩ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተዘጋጁ 11 የስልጠና ማዕከሎች እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን የአሰልጣኞች ስልጠናውን ቀደም ሲል በኢስኩል-ሲስተም አተገባበርና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ተመሳሳይ ስልጠና የወሰዱ የዘርፉ ባለሙያዎች በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአሰልጣኞች ስልጠናው ከኢስኩል ሲስተም አተገባበርና ተዛማች ጉዳዮች ጋር በተገናኘ በየትምህርት ቤቱ ለሚገኙ የአይ ሲቲ መምህራን ግንዛቤ በመፍጠር መምህራኑ በየትምህርት ቤቶቻቸው ለሚገኙ መምህራን ተመሳሳይ ግንዛቤ ፈጥረው ሲስተሙ በሁሉም ትምህርት ቤቶች በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ታስቦ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ አስታውቀዋል።

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና ማስፋፋት ቡድን መሪ አቶ ሚካኤል መስፍን የአሰልጣኞች ስልጠናው ለስድ ስት ቀናት እንደሚሰጥ ገልጸው መርሀግብሩም በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት እየተካሄደ እንደሚገኝ በመስክ ምልከታ ማረጋገጣቸውን አመላክተዋል።

0 Comments