(መስከረም 20/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮው የስነ ምግባርና ፀረ -ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት በሀብት ማስመዝገብ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች ሰጥቷል ::
ቀደም ሲል በሀብት ማስመዝገብ ላይ ግንዛቤ መፍጠር ሥራ መሰራቱን ያስታወሱት የቢሮው የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክተር አቶ አስራት ሽፈራው አሁን እየተካሄደ ካለ ሀብት ማስመዝገብ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የአረዳድ ክፍተቶችመስተዋላቸውን ጠቁመው ይህን ክፍተት ለማስተካከል ስልጠናው መዘጋጀቱን አብራርተዋል ::
ዳይሬክተሩ አያይዘውም የሀብት ምዝገባ መካሄዱ በመንግስት አሰራር ውስጥ ግልፅነትና ተጠያቂነት በማስፈን ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከል እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ማስፈን እንደሚቻል ተናግረዋል ::
አቶ አስራት በስልጠናው ላይ የሀብት ማስመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር 668/2002 አቅርበው አዋጁ የወጣበት አላማዎች ፣ የሀብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ ሕግ ጥቅሞች ፣ የምዝገባ አይነቶችና ንብረት ባለማስመዝገብ የሚከሰቱ ጉዳቶችንና መሰል ጉዳዮችን አብራርተዋል ::
አያይዘውም የሀብት ምዝገባ ቅፅ ይዘቶች ላይ ገለፃ አድርገዋል ::
0 Comments