(የካቲት 4/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለቢሮ ዳይሬክተሮች በ2017 በጀት ዓመት 6 ወራት የተከናወኑ የቁልፍ ውጤት አመላካች እቅድ አፈፃፀም ፣ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በሌብነትና ብልሹ አሰራር እንዲሁም ቅንጅታዊ አስራር አፈፃፀም ላይ ምዘና ለማድረግ የሚያስችል ኦረንቴሽን ለመዛኞች ሰጥቷል::
በኦረንቴሽኑ ላይ የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ ኃላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የቢሮው እቅድና በጀት ዳይሬክተር በአቶ ጌታሁን ለማና የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ፋንታሁን እያዩ የተገኙ ሲሆን በምዘናው አካሄድ ላይ ገለጻ ተደርጓል፡፡
በኦረንቴሽኑ ላይ የመመዘኛ መስፈርቶች ፣ የውጤት አሰጣጥና የመዛኝ ስነምግባርን አስመልከቶ የተዘጋጀ ሰነድ የቀረበ ሲሆን የቢሮ ሃላፊ አማካሪና የዘርፉ ሃላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ መዛኞች በተሰጠው ቼክሊስት መሰረት በእውቀትና በኃላፊነት ስሜት ከአድልዎ የፀዳና ስራን ማዕከል ያደረገ ምዘና እንዲያካሂዱ አሳስበዋል፡፡
0 Comments