(ህዳር 4/2017 ዓ.ም) በውይይቱ በቼክ ሊስቱ በተካተቱ የትኩረት ነጥቦች መሰረት ለሁለት ቀን በየትምህርት ቤቱ ተገኝተው ድጋፍና ክትትል የሚያካሂዱ ሱፐርቫይዘሮች እና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የዘርፉ አስተባባሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ ከሆኑ በሌሎች ትምህርቶች ውጤታማ የመሆናቸው እድል ከፍተኛ መሆኑን በመረዳት ቢሮው ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ወደ ትምህርት ቤቶች ማውረዱን ጠቁመው በተቋማቱ የሚካሄደው ድጋፍና ክትትል ስትራቴጂው ምን ያህል ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ በቼክ ሊስቱ በተቀመጡት ነጥቦች መሰረት የድጋፍና ክትትል ግኝቶቹን ግብረ መልስ በአግባቡ ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር መሀመድ በበኩላቸው ቀደም ሲል ተመሳሳይ ድጋፍና ክትትል በትምህርት ተቋማት መካሄዱን ገልጸው በድጋፍና ክትትሉ የሚቀርቡ ግኝቶች በቀጣይ ተማሪዎችን በሁለቱ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ ለማድረግ የተዘጋጀው ስትራቴጂ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።
በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ በትምህርት ተቋማት ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የተዘጋጀውን ቼክ ሊስት በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።
ተማሪዎችን በሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች ውጤታማ ለማድረግ የተዘጋጀው ስትራቴጂ በትምህርት ተቋማት ምን ያህል ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ በተዘጋጀ ቼክ ሊስት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
0 Comments