ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት እንደሚከበር የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።

by | ዜና

(ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም) “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን ፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሀሳብ የ2017 ዓ.ም 17ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የሚከበር መሆኑን የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።

በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መሪነት 17ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በፌደራል ፣ በክልሎችና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች ከተሞች በሚገኙ የመንግስት ተቋማት ፣ በትምህርት ቤቶችና በመከላከያ ሰራዊት ካምፖች ውስጥ በተመሳሳይ ሰዓት 4፡30 የሚሰቀል መሆኑ ተገልጻል፡፡

0 Comments