በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

by | ዜና

(ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም) ስልጠናው ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጡ የአይሲቲ ባለሙያዎችና መምህራን ጨምሮ ለሚኒ ሚዲያ ክበብ ተጠሪ መምህራን ከአዲስ አበባ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ አለም ወደ አንድ መንደር መምጣቷን በመገንዘብ አዲስ አበባን ስማርት ሲቲ ለማድረግ ባከናወናቸው ቴክኖሎጂን መ ሰረት ያደረጉ ተግባራት በአለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ማግኘቱን ጠቁመው የዚሁ አካል የሆነው እና በክብር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አማካይነት በመጣው 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ተጠቃሚ ከሚያደርጋቸው አካላት መካከል የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እንደሚገኙ አመላክተዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም የስልጠናው ተሳታፊዎች ተማሪዎች የኢኒሼቲቩ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከወዲሁ በየትምህርት ቤቱ በአግባቡ በመመዝገብ ልምምድ እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ቱሉ ጥላሁን 5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ፕሮግራም በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መንግስታት መካከል በተደረገ ስምምነት የተነደፈ የዲጂታል ክህሎት ስልጠና መርሀግብር መሆኑን ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት ገልጸው መርሀግብሩ ወጣቱ ትውልድ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ መሳተፍ የሚያስችለውን የዲጂታል ክህሎት እንዲኖረው ማስቻልን አላማው አድርጎ የተነደፈ ፕሮግራም መሆኑን አስረድተዋል።

0 Comments