በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የአንደኛ ሩብ አመት የሪፎርም ተግባራት አፈጻጸምን የተመለከተ የድጋፍና ክትትል ተግባር ተከናወነ።

by | ዜና

(ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ በቢሮው የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይራክቶሬት አማካይነት የተከናወነ ሲሆን ስራ ክፍሉ በትላንትናው እለት በድጋፍና ክትትል ተግባሩ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን መስጠቱ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይራክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ ከቡድን መሪው አቶ ሀፍቱ ብርሀኑ ጋር በጋራ በመሆን ድጋፍና ክትትሉ ከሚካሄድባቸው የትምህርት ጽህፈት ቤቶች መካከል በተወሰኑት ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል።

በድጋፍና ክትትሉ የተሳተፉ ባለሙያዎች በመስፈርቱ መሰረት የድጋፍና ክትትል ተግባሩን ማከናወናቸውን በምልከታ ሂደቱ ማረጋገጣቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይራክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ ጠቁመው ድጋፍና ክትትሉ የተቋማቱን የሪፎርም ስራ ውጤታማ ከማድረጉ ባሻገር በቀጣይ ለሚካሄደው የአንደኛ መንፈቅ አመት ምዘና ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዲችሉ ታስቦ መካሄዱን አመላክተዋል።

0 Comments