(ህዳር 20/2017 ዓ.ም) በውይይቱ የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ አተገባበርን አስመልክቶ በትምህርት ተቋማት ለሁለተኛ ዙር የተካሄደ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ በቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር መሀመድ እንዲሁም በተቋማቱ ከሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ አንጻር በአንደኛ ሩብ አመት ከተከናወኑ ተግባራት ጋር በተገናኘ የተካሄደ የክትትልና ድጋፍ ግብረመልስ ፍረጃ በሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ አማካይነት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ቢሮው ተማሪዎችን በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ ለማድረግ ባዘጋጀው ስትራቴጂ የተካተቱ 13 የትኩረት ነጥቦች በትምህርት ተቋማት ምን ያህል ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኝ በማረጋገጥ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ የድጋፍና ክትትል ስራ መከናወኑን ገልጸው ቢሮው በቀጣይ ጊዜያትም ትምህርት ቤቶች የደረሱበትን የአፈጻጸም ደረጃ አስመልክቶ የሚያካሂደውን የድጋፍና ክትትል ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ዶክተር ዘላለም አያይዘውም ከሪፎርምና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተገናኘ በትምህርት ቤቶች በተካሄደው የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ፍረጃ መሰረት አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ የሆኑ ተቋማትም ሆኑ በመካከለኛ ደረጃ የተቀመጡ ተቋማት በቀጣይ የተሻለ ስራ በመስራት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማጎልበት በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሊ ከማል በበኩላቸው ከሒሳብና እንግሊዘኛ ስትራቴጂ አተገባበርም ሆነ ከሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ አፈጻጸር ጋር በተገናኘ በትምህርት ተቋማት የተካሄደው የድጋፍና ክትትል ስራ የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል እንደመሆኑ የትምህርት ተቋማት በድጋፍና ክትትሉ በቀረቡ ግብረመልሶች በተቀመጡ የማስተካከያ ነጥቦች መሰረት በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስታውቀዋል።
የመርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች በሁለቱ ጉዳዮች በቀረቡ የግብረ መልስ ነጥቦች ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦችን እና ጥያቄዎችን አቅርበው በክፍለ ከተማና በቢሮ አመራሮች ምላሽ ተሰቷል።
0 Comments