በትምህርት ተቋማት ለሚደረግ ድጋፍና ክትትል በተዘጋጀ ቼክ ሊስት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

by | ዜና

(ህዳር 17/2017 ዓ.ም)ድጋፍና ክትትሉ በትምህርት ተቋማት ያለውን የኢ -ስኩል ሲስተም አተገባበር መሰረት አድርጎ በቢሮው የትምህርት ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት እና የመረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች እንዲሁም በክፍለ ከተማ የትምህርት ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የሚካሄድ ሲሆን የቢሮው የሲስተም ባለሙያ ወይዘሮ ፍሬህይወት ገብረአብ ለድጋፍና ክትትሉ የተዘጋጀውን ቼክ ሊስት አቅርበው ውይይት ተከሂዷል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዝርጋታና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ታዬ ወልደኪዳን ድጋፍና ክትትሉ ትምህርት ቤቶች የኢ -ስኩል ሲስተሙን በምን መልኩ ተግባራዊ እያደረጉት እንደሚገኙ በማየት በሚመጣው ግብረ መልስ መሰረት ተቋማቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመማር ማስተማር አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ለማድረግ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

0 Comments