በትምህርት ቤቶች የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችሉ ተገለፀ::

by | ዜና

(ጥር 19/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የመምህራንና የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድርን ለማስጀመር ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ውይይት አካሄዳል፡፡

             

በውይይቱ ላይ የተማሪዎች ስፖርት ሊግ ውድድር የማስጀመሪያ እቅድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ዲናኦል ጫላ የቀረበ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የስፖርት ሊግን አስመልክቶ ባወረደው አደረጃጀት መመሪያ መሰረት በሁሉም ትምህርት ቤቶች በክላስተር ተደራጅተው በተለያዩ የስፓርት አይነቶች የሚከናወኑ ስፖርታዊ ውድድሮችን አስመልክ ውጤታማ ስራ በቀጣይ ለመስራት እንዲቻል ውይይቱ ያግዛል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ወንድሙ ኡመር ውይይቱ ላይ እንዳሉት ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ትምህርት ቤቶች አይነተኛ መፍትሄ መሆናቸውን ጠቁመው ቢሮው በትምህርት ቤቶች ላይ እየተካሄዱ የሚገኙ ስፖርታዊ ውድድሮችን ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል:: አያይዘውም በክላስተር ደረጃ የሚካሄደው የተማሪዎችና መምህራን ስፖርት ውድድርም እስከ የካቲት 10 ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የቢሮው ማኔጅመንት አባላትን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ መምህራን የተሳተፉ ሆነዋል፡፡

0 Comments