(ታህሳስ 4/2017 ዓ.ም) በስልጠናው የክፍለ ከተማ እና ወረዳ ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ የክፍለከተማ የስራ አስተባባሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት የተቋማት ክትትልና ድጋፍ ስራ ክፍል በመጡ ባለሙያዎች ነው የተሰጠው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ስልጠናው በቅንጅታዊ አሰራር እና በመልካም አስተዳደር ጽንሰ ሀሳብ እንዲሁም አስፈላጊነትና አተገባበር ዙሪያ በየደረጃው ለሚገኙ ሱፐርቫይዘሮችና የስራ አስተባባሪዎች በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ተቋሙን በሪፎርም ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ ታስቦ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ጋር በጋራ መዘጋጀቱን ገልጸው የስልጠናው ተሳታፊዎች በቀጣይ እቅዳቸውን በመከለስ ወደ ተጨባጭ ተግባር መግባት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ በበኩላቸው ስራ ክፍሉ በቅርቡ ሱፐርቫይዘሮችን አሳትፎ ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ባካሄደው የድጋፍና ክትትል ግብረመልስ የሪፎርም ስራውን በአግባቡ ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር የተወሰኑ ክፍተቶች መኖራቸው በመለየቱ ስልጠናውን ማዘጋጀት ማስፈለጉን ጠቁመው ስልጠናው ከቅንጅታዊ አሰራርም ሆነ ከመልካም አስተዳደር ጋር በተገናኘ የነበሩ የአፈጻጸም ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን አመላክተዋል፡፡
0 Comments