(መስከረም 22/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ሰልጠና የወሰዱ የቢሮው ሰራተኞች በዛሬው እለት የተመረቁ ሲሆን በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የቢሮ ሰራተኞችና ስልጠናዉን የሰጡ መምህራን ተገኝተዋል፡፡
ስነ ስርዓቱ በሽማግሌዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የዘርፉ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ታጋቱ አባቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አፋን ኦሮሞ ቋንቋን በፍላጎታቸው ለመሰልጠን ፍቃደኛ ለሆኑ የቢሮው ሰራተኞች ስልጠናውን ሲሰጥ መቆየቱን በመጥቀስ ስልጠናዉን ለወሰዱ ስልጣኞች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
የሰራተኞች የሰልጠና ቆይታ አፋጻጸም ሪፖርት በአቶ ተሾመ ቀናሳ በቢሮ የአፋን ኦሮሞ ሰርዓተ ትምህርት ዳይሬክተር አማካኝነት የቀረበ ሲሆን ለተመራቂ ሰራተኞችና ለአሰልጣኝ መምህራን ሰርተፊኬት የመስጠት መርሀ ግብር ተከናውናል፡፡
በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ቢሮው የስልጠና መርሃ ግብሩን ሲያዘጋጅ በዋናነት ቋንቋን ማወቅ ተግባቦትን ከማስፋት ባለፈ ልሳነ ብዙህነት ለሁለንተናዊ ስኬት የራሱን በጎ ተፅዕኖ የሚያሳድር መሆኑን በመገንዘብ እንደሆነ ጠቁመው በቀጣይም ስልጠናውን የሚወስዱ ሰልጣኞችም ቢሮው ያመቻቸውን ዕድል በመጠቀም የቋንቋ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ጥሪ አቅርበዋል ::
ልሳነ ብዙህነት ለሁለንተናዊ ስኬት ላቅ ያለ ሚና እንዳለው ተገለጸ፡፡
0 Comments