ለክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤቶች የተካሄደው የ6 ወር የሪፎርምና የKPI ስራዎች አፈጻጸም ድጋፍና ክትትል ሪፖርት በቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል ፀደቀ።

by | ዜና

(ጥር 2/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ምዘና ዳይሬክቶሬት ለክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤቶች በሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ እና በKPI ላይ መሰረት ያደረገ ለሶስተኛ ጊዜ ድጋፍና ክትትል ያካሄደ ሲሆን የድጋፊና ክትትሉን ሪፖርት ፣ ግብረ መልስና ፍረጃን የቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል ውይይት በማድረግ አጽድቋል።

            

ድጋፍና ክትትሉ በመደበኛ እንዲሁም በሪፎርም ስራዎች ስኬታማ የስራ አፈጻጸም መኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ፈንታሁን እያዩ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

የቢሮ ሀላፊ አማካሪና የዘርፉ ሀላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በ11ዱም ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች ያሉ ስራዎች ወጥ የሆነ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ብሎም ተገቢ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖሩን በማየት ክፍተት ያለበትን የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ለመደገፍ እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡ ድጋፍና ክትትል ተግባሩ በዚህ በጀት አመት ለሶስተኛ ጊዜ የተከናወነ መሆኑን ያነሱት ሀላፊዋ በቀጣይ ለሚደረግ የምዘና ስራ የማንቃትና የተግባር ምእራፍ አፈጻጸምን ለማየት እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም የቀረበዉ ሪፖርት በክፍል እንዲሁም በዘርፍ ደረጃ ተገምግሞ ለቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል ለውይይት የቀረበና የጸደቀ መሆኑን ገልጸዋል።

0 Comments