ለክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤቶች የተካሄደው የ6 ወር የሪፎርምና የKPI ስራዎች አፈጻጸም ድጋፍና ክትትል ሪፖርት ተገመገመ።

by | ዜና

(ጥር 2/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ምዘና ዳይሬክቶሬት ለክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤቶች በሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ እና በKPI ላይ መሰረት ያደረገ ለሶስተኛ ጊዜ ድጋፍና ክትትል ያካሄደ ሲሆን የድጋፊና ክትትሉን ሪፖርት ፣ ግብረ መልስና ፍረጃ በዘርፍ ደረጃ ተገምግሞ ለቢሮ ጀነራል ካውንስል ለውይይትና ለውሳኔ እንዲቀርብ ተደርጋል።

የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ፈንታሁን እያዩ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ድጋፍና ክትትሉ በመደበኛ እንዲሁም በሪፎርም ስራዎች ስኬታማ የስራ አፈጻጸም መኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቢሮ ሀላፊ አማካሪና የዘርፉ ሀላፊ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በ11ዱም ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤቶች ያሉ ስራዎች ወጥ የሆነ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ብሎም ተገቢ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖሩን በማየት ክፍተት ያለበትን የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ለመደገፍ እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡ ድጋፍና ክትትል ተግባሩ በዚህ በጀት አመት ለሶስተኛ ጊዜ የተከናወነ መሆኑን ያነሱት ሀላፊዋ በቀጣይ ለሚደረግ የምዘና ስራ የማንቃትና የተግባር ምእራፍ አፈጻጸምን ለማየት እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም የቀረበዉ ሪፖርት በክፍል እንዲሁም በዘርፍ ደረጃ ተገምግሞ ለቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል እንደሚቀርብና እንዲጸድቅ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

0 Comments