(ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም) የገና ፆም ከቤተ ክርስቲያን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የሚፆሙት ታላቅ ፆም ነው። ዛሬም ክርስቲያኖች ይህንን ፈለግ ተከትለው በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የሚያስቡበት ነው።
ይህንንም ታላቅ የፆም ወቅት በማጠናቀቅ ለዛሬ ው የገና በዓል ዋዜማና በነገው እለት ለሚከበረው የገና በዓል ላደረሳችሁ ላደረሰን ለፈጣሪ ክብር ምስጋና ይድረሰው።
በዓሉን ስናከብር ያለንን ተካፍለን ፣ አቅመ ደካምችንና አረጋዊያንን አግዘን እንዲሁም ለሌሎች ብርሀን በመሆን፣ ወንድማማችነትን በማጎልበት ፣ ፍቅርን በማብዛት እና እርስ በእርስ በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል።
በመጨረሻም ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን ! እያልኩ በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የመረዳዳት፣ የሰላም ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆን ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡
አመሰግናለሁ!
ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ
0 Comments