(ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም) በግምገማ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፈ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ የመድረኩ ዋና አላማ ውጤታማ ስራዎችን በማጎልበት የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ 6 ወራት እቅድ ውስጥ በማካተት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር ለማገዝ መሆኑን ተናግረዋል።
ሀላፊዉ አክለዉም የግምገማ መድረኩ ያሉንን ጥንካሬዎች በማስቀጠልና ክፍተቶቻችን ላይ ጠንክሬን በመስራት የተሻለ ዜጋ ለመፍጠርና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እንድንችል ይረዳናል ብለዋል።
በመድረኩ በዘርፉ ስር የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች እቅድ አፈፃፀማቸዉን አቅርበዉ ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና በቀሪ 6 ወራት ውስጥ መሰራት በሚገባቸው ነጥቦች ላይ አቅጣጫ ተቀምጣል።
0 Comments