(ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ሀፍቱ ብርሀኑ በ1ኛ ሩብ አመት ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት ጋር በጋራ የተከናወኑ የቅንጅታዊ አሰራርና መልካም አስተዳደር ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።
በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት ከ28 ተቋማት ጋር 31 ዋና እና 146 ንዑሳን ተግባራትን በመለየት የስምምነት ፊርማ በመፈራረም ወደ ተግባር ተገብቶ የተለያዩ ውጤታማ ስራ መሰራታቸው በሪፖርቱ ቀርቧል።
የትምህርት ልማት ስራው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ የሚችለው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ሲቻል በመሆኑ ቢሮው በ2017 ዓ.ም ከሴክተር መስሪያ ቤቶችም ሆነ የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር የስምምነት ፊርማ ተፈራርሞ ውጤታማ ስራ መስራቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጠቁመው በአንደኛ ሩብ አመት በቅንጅታዊ አሰራሮች የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራትን አጠናክሮ በመቀጠል የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር የማሻሻል ሂደቱን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል።
የቢሮው ማኔጅመንት አባላት በ2017 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት ጋር በጋራ የተከናወኑ የቅንጅታዊ አሰራርና መልካም አስተዳደር ተግባራት አፈጻጸምን ገመገሙ።
0 Comments