የስኩል ኔት መሰረተ ልማት ኦፕቲማይዜሽን ስራ ለተሰራላቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ።

by | ዜና


(ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም) ስልጠናው የኦፕቲማይዜሽኑ ስራ ከሰራው ኒው ዌቭ ሀይ ቴክ ሶሉሽን በመጡ ባለሙያዎች እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በስልጠናው ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት የሚገኙ የአይ ሲቲ ባለሙያዎችን ጨምሮ የኦፕቲማይዜሽኑ ስራው በተሰራባቸው 74 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ የአይ ቲ መምህራን እና የክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች ተሳታፊ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኔትወርክ አስተዳደር ባለሙያ አቶ መርጋ አሰበ አስታውቀዋል።

የስኩል ኔት መሰረተ ልማት ኦፕቲማይዜሽን ስራ ከተማ አስተዳደሩ በመደበው ከፍተኛ በጀት የተሰራ እንደመሆኑ መሰረተ ልማቱ የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያግዝ ስልጠና መሆኑን የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን መሰረተ ልማት ዝርጋታና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ታዬ ወልደኪዳን ገልጸው ስልጠናው መሰረተ ልማቶቹን እንዴት መጠቀም እንደሚቻልና የመሳሪያዎች ብልሽት ቢያጋጥም በምን መልኩ ጠግነው አገልግሎት ላይ ማዋል እንደሚችሉ ክህሎታቸውን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑንም አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በበኩላቸው የስኩል ኔት መሰረተ ልማት የኦፕቲማይዜሽን ስራ መሰረተ ልማቱ የሚፈለገውን አገልግሎት እንዲሰጥ ከማስቻሉ ባሻገር በኢ-ስኩል ሲስተም ውስጥ ያሉ ሞጁሎችን በአግባቡ ለመተግበር ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር አመላክተዋል።

0 Comments