(ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና እስታንዳርዳይዜሽን አስተባባሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ይመርና የትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበበ ቸርነት ቢሮ ባካሄደው የመጀመሪያ ረብ ዓመት የሪፍርም ስራዎች አፈፃፀም ክፍሉ ድጋፍ ከሚሰጡ ዳይሬክቶሬቶች መካከል የተሻለ ውጤት ያስመዘገበበትን ሂደት ከእቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ፤ ሰነዶችን የመሰነድ ዘዴዎችና ሌሎች የአሰራር ሂደቶችን የያዙ ሰነዶች ፣ ቲም ስፕሪት ፈጥሮ ከመስራት አካያ ፣ የተናበበ ሰራና ሲስትም ፈጥሮ ከመስራት አኳያ የተከናወኑ ተግባራትና በተከናወኑ ስራዎች የተገኙ ውጤቶችን በማቅረብ ልምዳቸውን አካፍለዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና እስታንዳርዳይዜሽን አስተባባሪ ወ/ሮ ሰላማዊት ይመር የቀረበው ሰነድ ስራችንን በምናከናውንበት ወቅት ወስደን ልንጠቀምበትና አገልግሎት አሰጣጣችንን በውጤታማነት ለማከናወን ያግዛል ያሉ ሲሆን የቀረበዉን መነሻ በማድረግ የተሻለና የተቀራረበ አፈጻጸም እንዲኖር በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
0 Comments