የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ።

by | ዜና

(ታህሳስ 19/2017 ዓ.ም) በግምገማው የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የሪፎርም ስራ አስተባባሪዎችን ጨምሮ የቢሮው የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ በ2017ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቅ አመት የአገልግሎት አሰጣጥን እና የቅንጅታዊ አሰራርን ጨምሮ አጠቃላይ የሪፎርም ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ባከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆኑን አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም ስራ ክፍሉ በየደረጃው ለሚገኙ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን በመስጠት ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የአንደኛ ሩብ አመት የሪፎርም ተግባራት አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ የድጋፍና ክትትል ስራ መሰራቱን ገልጸው የድጋፍና ክትትል ግብረ መልሱን መሰረት በማድረግ የተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ በመፈረጅ ሪፖርት መደረጉን አመላክተዋል።

በመርሀ ግብሩ የቢሮው የሪፎርም ስራዎች ሪፖርት እና በክፍለ ከተማ ደረጃ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ ከአንደኛ መንፈቅ አመት እቅድ አፈጻጸም ጋር በተገናኘ በሚከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ምዘና ሂደት ጋር በተገናኘም ውይይት ተካሂዷል።

0 Comments