የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ለምክትል ርዕሳነ መምህራን ስልጠና ሰጠ።

by | ዜና

(ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በተከታታይ የሙያ ማሻሻያ(ተሙማ) መርሀ ግብር አተገባበርን መሰረት አድርጎ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመምህራን ልማት ምክትል ርዕሳነ መምህራን መሰጠቱን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ ስልጠናው በዋናነት በትምህርት ቤቶች ወጥ የሆነ ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ(ተሙማ) መርሀ ግብር ተግባራዊ እንዲሆን ዘርፉን የሚመሩ ምክትል ርዕሳነ መምህራን በቂ ግንዛቤ ፈጥረው መርሀ ግብሩን በአግባቡ ተግባራዊ እንዲያደርጉ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በስልጠናው ከተከታታይ የሙያ ማሻሻያ መርሀ ግብር ባሻገር ከአዲስ ጀማሪ መምህራን(አጀመ) ጋር በተገናኘም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው መሰጠቱን ጠቁመው የስልጠናው ተሳታፊዎች ከመርሀ ግብሮቹ አተገባበር ጋር በተገናኘ ያገኙትን ግንዛቤ መ ሰረት በማድረግ የተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር እንዲሻሻል የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ስልጠናውን የቢሮው የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ቀናሳ እንዲሁም የክፍለ ከተማ ሱፐርቫይዘር የሆኑት አቶ ታምሩ ሁጂሶ መስጠታቸውን የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

0 Comments