ዜና

በሰላማዊ መማር ማስተማር ዙሪያ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት ተካሄደ።
(ህዳር 21/2016 ዓ.ም) ውይይቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን በውይይቱ በሰላማዊ የመማር ማስተማር አተገባበርን በተመለከተ የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ በአቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ...

የ2016 ዓ.ም የትምህርት ቤቶች የጽዳት ንቅናቄ ማስጀመያ መርሀ- ግብር በእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ተጀመረ፡፡
(ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም) በንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ- ግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ አመራሮች እንዲሁም የጉለሌ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽህፈት ቤት አመራሮች ፤ መምህራን እና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማ በመርሀ- ግብሩ መክፈቻ...

ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት! በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ በተማሪዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የጥያቄና መልስ ውድድር ተጠናቀቀ።
(ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም) በዛሬው የማጠቃለያ ውድድር ቀደም ሲል ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳ ፣ ክፍለ ከተማና ከተማ ደረጃ በተካሄደ ውድድር አሸናፊ የሆኑ አምስት ከአማርኛ አምስት ከአፋን ኦሮሞ በድምሩ 10 የሰባተኛ እና ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ውድድሩም በዋናነት ህገ-መንግስትና የፌደራሊዝም ስርዓትን መሰረት አድርገው በተዘጋጁ ጥያውቄዎች ላይ መሰረት በማድረግ ነው የተካሄደው ። የአዲስ አበባ...

በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተዘረጉ የስኩል ኔት መሰረተ ልማቶችን በአዲስ መልክ ስራ ለማስጀመር የሚያስችል የመስክ ምልከታ (sight survey) በመካሄድ ላይ ነው።
(ህዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም) የስኩል ኔት ፕሮጀክቱ ከ10 አመት በፊት ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት መማር እንዲችሉ ታስቦ በወቅቱ በነበሩ 74 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተዘረጋ ሲሆን መሰረተ ልማቱ ዳግም ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል ኒው ዌቭ ሀይቲክ ሶሉሽን የተሰኘ ድርጅት ጨረታ በማሸነፍ ጥገናን ጨምሮ የጎደሉ እቃዎችን ለማሙዋላት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር መፈራረሙ ይታውቃል። የአዲስ አበባ...

የመምህርነት የስራ ቅጥር ማስታወቂያ! (ህዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም)
ለመመዝገብ ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdxUL1wAfiSGg1hOhpblCLTOqFHFBu3Iu2nx-R401Opy8525g/viewform ማሳሰቢያ ምዝገባ በአካል የማይከናወን ሲሆን ከላይ በተገለፀው ማስፈንጠሪያ ላይ ብቻ የሚፈፀም...

ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ በተማሪዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ።
(ህዳር 18 ቀን 2016 ዓ.ም) የዛሬው ውድድር ሀሙስ ለሚካሄደው ከተማ አቀፍ የማጠቃለያ ውድድር የሚያልፉ አምስት ከአማርኛ አምስት ከአፋን ኦሮሞ በድምሩ 10 ተማሪዎች የሚለዩበት የማጣሪያ ውድድር ሲሆን በውድድሩ ከየክፍለከተማው አሸናፊ ሆነው የቀረቡ 22 ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። የጥያቄና መልስ ውድድሩ ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ ህገመንግስትና ፌደራሊዝም ስርአትን መሰረት ባደረጉ ጥያቄዎች በተካሄደ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ “ብዝሀነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት ” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት ከትምህርት ቤት ጀምሮ በየደረጃው ሲያካሂድ የነበረውን የፓናል ውይይት በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡
(ህዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም) ውይይቱ ዛሬ በቢሮ ደረጃ ሲጠቃለል የቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር አመራሮችእና የወላጅ ማህበር ተወካዮች ፣ የትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ሰራተኞች ፣ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን በመርሀ-ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ...

አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀውን የክወና እና የእይታ ጥበባት (performing and visual art)ትምህርት ለሚያስተምሩ መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
(ቀን ህዳር 16/2016 ዓ.ም) በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተመለመሉና ከሙዚቃ ትምህርት ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ የሌላቸው መምህራን የተሳተፉ ሲሆን መምህራኑ በዚህ ስልጠና ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት አድርገው በየትምህርትቤታቸው ለሌሎች መምህራን በተመሳሳይ ሁኔታ ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባር የሚያከናውኑ ይሆናል። ስልጠናው በዋናነት መምህራኑ ለትምህርት አይነቱ የተዘጋጀውን የመጽሀፍ ይዘት በአግባቡ...

በአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት(GEQIP-E)ከ2010 እስከ 2015ዓ.ም ለአምስት አመታት የተከናወኑ ተግባራት ግምገማ ተካሄደ።
(ቀን ህዳር 16/2016 ዓ.ም) ግምገማው በዋናነት አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት (GEQIP-E) ፕሮግራም ትግበራ ከተጀመረበት ከታህሳስ 2010 ዓ.ም እስከ 2015 በጀት አመት ድረስ የተከናወኑ ተግባራትን በተለይም የውስጥ ቅልጥፍና ከማሻሻል ፣የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ፣ የትምህርት ፍትሀዊነትና ተደራሽነትን እንዲሁም የተሻሻለ የአስተዳደር አቅም ከማጎልበት...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ለአምስት ቀን ሲሰጥ የቆየውን የአሰልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡
(ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም) የአሰልጣኞች ስልጠናው ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ካሉ መዋቅሮች ለተውጣጡ ባለሙያዎች ቡድን መሪዎች አስተባባሪዎች በሁለት ቡድን ለ68 ሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን ዳይሬክተሮች አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች አንድ ላይ እንዲሁም ባለሙያዎች በሌላ ቡድን የአሰልጣኞች ስልጠናውን እንዲወስዱ ተደርጉዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ...