አማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ መምህራኖች ስልጠና ተሰጠ ::

አማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ መምህራኖች ስልጠና ተሰጠ ::

(ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ  ጋር በመተባበር አማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎችን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለሚያስተምሩ መምህራኖች  የ2ኛ ቋንቋ የመማር ማስተማር ስነ ዘዴና ስትራቴጂ ፣ የ2ኛ ቋንቋን የመማር ማስተማር ክህሎት እና የ2ኛ ቋንቋን በልምምድ ማስተማር የሚያስችላቸው ስነ ዘዴዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት ጀምራል...
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመምህራን ስልጠና መስጠት ጀመረ ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመምህራን ስልጠና መስጠት ጀመረ ::

(ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር  ለስራና ተግባር ትምህርት (CTE) መምህራን ለሶስት ሳምንታት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀምሯል :: ስልጠናው የስራና ተግባር ትምህርት (CTE) መምህራን በት/ት ቤቶች ሊተገብሯቸው ስለሚገቡ የማስተማር ስነ-ዘዴ እና ስትራቴጂዎች ፣ የምዘና ስርአት ፣ የክፍል ውስጥ መማር ማስተማር ሂደት አስተዳደር እና...
ቢሮው በ2017 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት ከተለያዩ  ተቋማት ጋር በጋራ ያከናወናቸውን የቅንጅታዊ አሰራርና የመልካም አስተዳደር ተግባራት አፈጻጸም ገመገመ።

ቢሮው በ2017 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ያከናወናቸውን የቅንጅታዊ አሰራርና የመልካም አስተዳደር ተግባራት አፈጻጸም ገመገመ።

(ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ ከቢሮው ጋር በትስስር የተለያዩ ተግባራት ከሚያከናውኑ ተቋማት የመጡ ኃላፊዎችና ተወካዮችን ጨምሮ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም በትምህርት ሴክተሩ የድጋፍና ክትትል ተግባር የሚያከናውኑ የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ፣የከንቲባ ጽህፈት ቤት እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ...
የተማሪዎች መምህራንና መጋቢ እናቶች የደንብ ልብስ ስርጭት አፈጻጸምን አስመልክቶ ግምገማ ተካሄደ፡፡

የተማሪዎች መምህራንና መጋቢ እናቶች የደንብ ልብስ ስርጭት አፈጻጸምን አስመልክቶ ግምገማ ተካሄደ፡፡

(ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ፤ መምህራንና መጋቢ እናቶች ደንብ ልብስ ስርጭት አፈጻጸምን በተመለከተ ከመንግስት ግዢ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ቢሮ እና 18 አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከደንብ ልብስ አቅራቢዎቹ ጋር ባደረጉት ውይይት ከስርጭት ጋር በተየያዘ...
የቢሮው ማኔጅመንት አባላት በ2017 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት ጋር በጋራ የተከናወኑ የቅንጅታዊ አሰራርና መልካም አስተዳደር ተግባራት አፈጻጸምን ገመገሙ።

የቢሮው ማኔጅመንት አባላት በ2017 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት ጋር በጋራ የተከናወኑ የቅንጅታዊ አሰራርና መልካም አስተዳደር ተግባራት አፈጻጸምን ገመገሙ።

(ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ሀፍቱ ብርሀኑ በ1ኛ ሩብ አመት ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት ጋር በጋራ የተከናወኑ የቅንጅታዊ አሰራርና መልካም አስተዳደር ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል። በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት ከ28 ተቋማት ጋር 31 ዋና እና 146 ንዑሳን ተግባራትን በመለየት የስምምነት ፊርማ...
የመሰረታዊ ጎልማሶች ትምህርት መጽሐፍ ትውውቅ ተደረገ ::

የመሰረታዊ ጎልማሶች ትምህርት መጽሐፍ ትውውቅ ተደረገ ::

(ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ማዕቀፍ መሰረት በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የተዘጋጀ የጎልማሶች መማሪያና አመቻች መምሪያ መጽሃፍት ትውውቅ አድርጓል፡፡ በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የተዘጋጁት የጎልማሶች መማሪያና አመቻች መምሪያ መጽሃፍት ጎልማሶች የማንበብ ፣...