ዜና

በእቅድ ዝግጅት ፤ በመልካም አስተዳደርና ቅንጅታዊ ስራዎች ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
(ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬትና የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት በጋራ በመሆን በእቅድ አዘገጃጀትና ሪፖርት ፤ በአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በክትትልና ድጋፍ አሰጣጥ ላይ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ ኃላፊ ወ/ሮ...

የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት በአንደኛ ሩብ አመት በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸምን ገመገመ።
(ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ በየደረጃው የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች የተሳተፉ ሲሆን በተመረጡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ክላስተር ማዕከላት የአማርኛ እና የአፋን ኦሮሞ የሱፐርቪዥን ሪፖርት በተወካዮች ከመቅረቡ ባሻገር የቢሮው የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። በአንደኛ ሩብ አመት በትምህርት ቤቶች በተካሄደ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በየደረጃው የተከናወኑ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በደሞዝ ማስተካከያ አፈፃፀም መመሪያ ላይ በቢሮው ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችና ለአዳሪ ትምህርት ቤቶች ኦረንቴሽን ሰጠ::
(ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በደሞዝ ማስተካከያ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ በሰጠው ኦረንቴሽን መሰረት በቢሮው መካሄድ ስላለበት ቅድመ ዝግጅትና በማስፈፀም ሂደት ውስጥ በሚጠበቁ ጉዳዮች ላይ በቢሮ ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች እና ቡድን መሪዎች እንዲሁም ለእቴጉ መነን የሴት ተማሪዎች አዳሪ ትምህርትቤትና ለገላን የወንዶች አዳሪ...

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።
(ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም) በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል። ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር...

ለቢሮው የስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች በኢ-ስኩል ሲስተም አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
(ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም) ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት እና ሲስተሙን ባለማው ትሪያ ትሬዲንግ በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን በቢሮው የኢንፎረሜሽን ኮሚኒኬሽን የሶፍት ዌርና ዳታ ማዕከል ቡድን መሪ ወይዘሮ ሰላም ተስፋዬ አማካይነት በሲስተሙ ስለተካተቱ ስድስት ሞጁሎች ገለጻ ተደርጉዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ...

የአንደኛ ሩብ አመት ሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም ድጋፍና ክትትል ተደረገ።
(ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ምዘና ዳይሬክቶሬት በቢሮው ለሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች በሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ድጋፍና ክትትል ማድረጉን አሳውቋል፡፡ ድጋፍና ክትትሉ በመደበኛ እንዲሁም በሪፎርም ስራዎች ስኬታማ የስራ አፈጻጸም መኖሩን የስራ ክፍሉ የሚያረጋግጥበት አንዱ መንገድ መሆኑን የገለጹት የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪ ወላጆች ማህበር (ተወማህ) የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲጎለብት የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።
(ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም) ማህበሩ የ2017 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸሙን የከተማው የተማሪ ወላጆች ማህበር(ተወማህ) ምክር ቤት አባላት በተገኙበት ገምግሟል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና ግብአት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀጸላ ፍቅረማርያም በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል የሚያከናውናቸው...

የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የዘርፉን የ2017 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ።
(ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የክፍለ ከተማ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የዳይሬክቶሬቱ እና የተመረጡ ክፍለ ከተሞች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በዘርፉ በ2017 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ በመወያየት በቀጣይ የተሻለ ስራ...

በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
(ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም) ስልጠናው ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጡ የአይሲቲ ባለሙያዎችና መምህራን ጨምሮ ለሚኒ ሚዲያ ክበብ ተጠሪ መምህራን ከአዲስ አበባ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በጋራ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ አስታውቀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ...

የከንቲባ ፅ/ቤት መልካም አስተዳደርና አቤቱታ ዘርፍ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመገኘት ድጋፍና ክትትል አደረገ::
(ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም) የከንቲባ ፅ/ቤት መልካም አስተዳደርና አቤቱታ ዘርፍ ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመገኘት የ2017 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ አቀራረብና አፈታት ሥራዎች ላይ ድጋፍና ክትትል አድርጓል :: ቡድኑ በድጋፍና ክትትሉ የተለያዩ በቪዲዩ በፎቶና በወረቀት የተሰነዱ ሰነዶችን የተመለከተ ሲሆን ቢሮው በሩብ ዓመቱ ያከናወነው አፈፃፀም አመርቂ...