አገልግሎቶች
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡-
ስለ እያንዳንዱ አገልግሎት ዝርዝር መረጃ ለማወቅ ከታች ይመልከቱ፡፡
የቀዳማይ ልጅነት ክብካቤ ዝግጅትና ትግበራ
- የቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ክብካቤ ዝግጅት
- የቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ክብካቤ ስልጠና
- የቀዳማይ ልጅነት ሞዴል ትምህርት ተቋማት መፍጠር፣
- የቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ትግበራ ክትትል፣
- ጥናትና ምርምር
የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች
- በስርአተ ፆታ ማስረጽ
- በስርአተ ፆታ ጉዳይ ላይ የግንዛቤ ደረጃ ዳሰሳ ማካሄድ
- የስርአተ ፆታ የባህሪ ለውጥ ግንዛቤ ክፍተትን ለመሙላት ስልጠና ማካሄድ፣
- በስርአተ ጾታ ሜንስትሪሚንግ ላይ የአጋርነት ተግባራትን ማከናወን፣
- የስርአተ ጾታ ተግባራት አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ማድረግ፣
- የስርአተ ጾታ ተፅዕኖ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፣
- የነጭ ሪቫን ቀን ፓናል ማዘጋጀትና ማክበር
- የእናቶች ቀን ፓናል ውይይት ማዘጋጀትና ማክበር፣
- የኤች.አይ.ቪ /ኤድስመከላከልና መቆጣጠር
- የኤች.አይ.ቪ /ኤድስ ተጋላጭነት ጥናት
- በኤች አይቪ ኤድስ ሜንስትሪሚንግ ላይ የአጋርነት ተግባራትን ማከናወን፣
- በኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር የግንዛቤ ስልጠና መስጠት፣
- አለም አቀፍ የኤች አይቪ/ኤድስ ቀንን ማክበር
- ከአደንዛዥ እፆች፤ ከአደገኛ ሱሶችና ከአቻ ግፊት እንዲጠነቀቁ የህይወት ክህሎት ትምህርት የሚሰጥበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት
ድጋሚ ማስረጃ ቅድመ ሁኔታዎች
ድጋሚ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ አገልግሎት ለማግኝት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡-
- ማንነትን የሚገልጽ ህጋዊ መታወቂያ ይዞ መቅረብ
- ከፖሊስ የጠፋበት አፅፎ ማቅረብ አለበት
- ከአንድ ዓመት ወዲህ የተነሱትን 3×4 የሆነ ፎቶ ግራፍ
- ጠያቂው ወይም ህጋዊ ወኪል በአካል መቅረብ ይገባዋል
- ከላይ የተገለጹት ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ 100.00 ብር በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል
የስም ስህተት ለማስተካከል ሟሟላት ያለበት
- ልደት ካርድ ኮፒና ዋናውን
- ትራንስክሪብት ከ9 – 10 ወይም 11 – 12 ዋናውንና ኮፒ
- የታደሰ የቀበሌ መታወቅያ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ኮፒ
- የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውን
- 1 ፎቶ ግራፍ እና 100.00 ብር
የትምህርት ቤት ስታንዳርድ
- የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም የደረጃ መለኪይ/Standrad/ —– ዳዎንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
- የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የደረጃ መለኪያ/Standrad/ —– ዳዎንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
- የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መለኪያ/Standrad/ —– ዳዎንሎድ ለማድረግ እዚህ ይጫኑ
የአቻ ግመታ ቅድመ ሁኔታዎች
የአቻ ግመታ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች :-
- የትምህርት መረጃውን በተማሩበት አገር የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቦርድ ወይም District of education /council/ በጀርባው ላይ የባለስልጣኑ ስም፣ ቲተርና ማህተም እንዲሁም በተማሩበት ሀገር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህተምና ፊርማ የተረጋገጠ መሆን አለበት
- የትምህርት መረጃው ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ውጪ የተጻፈ ከሆነ በኢትዮጵያ ህጋዊ መተርጎም ፈቃድ ባላቸው ድርጅቶች የተተረጎመና በተርጓሚው ድርጅት ማህተም የተረጋገጠ መሆን ይገባዋል ፡፡
- በትምህርት መረጃው የፈተና ውጤቶች በፊደል ወይም በቁጥር ከተሰጡ ምን ማለት እንደሆነ አቻ መገለጫ ያለው መሆን አለበት
- የትምህርት መረጃና የሌሎች ማስረጃዎች ዋናና አንዳንድ ፎቶ ኮፒ መቅረብ አለበት
- መረጃ ጠያቂው ወይም ህጋዊ ወኪል በአካል መቅረብ ይኖርበታል
- ከላይ የተገለጹት ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ 150.00 ብር በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት ይቻላል ፡፡
የተቋማት ጥራት ኦዲት
ተቋማት የጥራት ኦዲት እንዲደረግላቸው የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች ይጠበቁባቸዋል፡-
- በተላከላቸው ቅጽ መሠረት የውስጥ ግምገማ ያደረጉበት ሪፖርት፣
- ተቋሙ እውቅና/የዕድሳት የፈቃድ ማረጋገጫ
- የተቋሙ ስም የትምህርት ደረጃ/መስክ