ቀን 16/07/2014 ዓ.ም

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት የ1ኛ ወሰነ ትምህርት በ12ኛ ክፍል ፈተና በፈተና ጥያቄዎች ውጤታማነት ላይ ትኩረት ያደረገ ምክክር አካሄደ።

በምክክር መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ እንደገለጹት የውጤት ትንተናው ያሉ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ለመስጠትና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ያስችላል ብለው የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ነው ብለዋል። አክለውም የተጀመረውን የውጤት ትንተና በማጠናከር የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዳኘው የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በሚሰሩ ስራዎች ላይ ሁሉም ዜጋ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት እጅጋየሁ አድማሱ በበኩላቸው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደ ክ/ከተማ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀው የዛሬው ውጤት ትንተናም በፈተና አወጣጥና አሰጣጥ ሂደት ያሉ ክፍተቶችን በመለየትና ለክፍተቶች መፍትሄ በመስጠት የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-መግባር ለማሻሻል ያስችላል ብለዋል።

በጽ/ቤቱ የስርዓተ ትምህርት ትግበራና ክትትል ቡድን መሪ አቶ ገዳ ሞሲሳ በበኩላቸው የተማሪዎችን ውጤትና ስነ-መግባር ለማሻሻል በርካታ ተግባራትን አከናውነናል ብለው የዛሬው ትንተናም የውጤትና ስነ-መግባር ማሻሻያው አካል ነው ብለዋል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry