ቀን 09/07/2014 ዓ.ም

”ትምህርት ቤቴን አጸዳለሁ፣ ጽዱና ውብ በሆነ ትምህርት ቤት እማራለሁ” በሚል መሪ ቃል ሁሉን አቀፍ የጽዳት ንቅናቄ በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ በይማነ ብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በይፋ ተጀምሯል፡፡

ንቅናቄው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፣የክፍለ ከተማና ወረዳ ኃላፊዎች እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በተገኙበት በዛሬው እለት ተጀምሯል።

የፅዳት ንቅናቄውን ያስጀመሩትየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ትምህርት ቤቶች ውብና ምቹ መሆን አለባቸው በመሆኑም ትምህርት ቤታችሁን በማፅዳት ሂደት ውስጥ የኛም እገዛ ይታከልበታል ሲሉ ገልፀው የግቢውን መሰረተ ልማት ለመገንባት ቃል ገብተዋል።

ለ3ወራት በሚቆየው የትምህርት ቤቶች የፅዳት ንቅናቄ ጠንካራ ተሳትፎ አድርጋችሁ በሽልማት እንገናኝ ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ጠንክራቹ ተምራቹ ቤተሰብና ሀገራችሁን ማኩራት አለባችሁ የሚል መልክት አስተላልፈዋል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry