ቀን 06/07/2014 ዓ.ም
ጎሮ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመምህራን ልጆች ማቆያ (day care) አስመረቀ ::
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ጎሮ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመምህራን ልጆች ማረፊያ ይሆን ዘንድ ያዘጋጀውን ክፍል የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባዩማ ወርቁ በተገኙበት አስመርቃል።
ወ/ሮ ባዩማ በምርቃት ሥነ -ስርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የጎሮ ትምህርት ቤት ከዚህም በፊት ብዙ ስራዎችን እየሰራ ያለ ተቋም ነው በተለይም የመምህራን ልጆች ማረፊያ (Day care) አንዱ ማሳያ ነው በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ቢኒያም ሽመልስ ለመምህራን ልጆች ማረፊያ ስናስመርቅ ለስራቸው ሳይቸገሩ ልጆቻቸውን በቅርብ ሁነው እየተከታተሉ የመማር ማስተማር ሂደቱን ማሳለጥ ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል ።