ቀን 29/6/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ትግበራ ዳይሬክቶሬት የኢንፎረሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን በስኩል ኔት መሰረተ ልማት አጠቃቀምና ተዛማች ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

በውይይቱ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎችን ጨምሮ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ውይይቱ በዋናነት በ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአንደኛ መንፈቅ አመት በየትምህርት ቤቱ የፕላዝማ ትምህርት አሰጣጥ ሂደትን ጨምሮ የአይ ሲቲ ላብ እና የኢንተርኔት አጠቃቀም ጋር የተገናኙ ሂደቶች ላይ መወያየትን መሰረት አድርጎ መዘጋጀቱ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት ከፍተኛ በጀት በመመደብ በየትምህርት ቤቶቹ የስኩል ኔት መሰረተ ልማቶችን ዘርግቶ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት እንዲያገኙ ለማስቻል በየትምህርት ቤቱ የአይ ሲ ቲ ባለሙያዎችን ከመመደብ ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ይሁን እንጂ በየትምህርት ቤቱ መሳሪያዎቹን በአግባቡ ከመጠቀም አንጻር የሚታዩ ችግሮች መኖራቸውን በመጥቀስ መሰረተ ልማቱ የሚፈለገውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል ርዕሳነ መምህራን ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በውይይቱየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ በለጠ ንጉሴ በአንደኛው መንፈቅ አመት በየትምህርት ቤቱ ስለነበረው የስኩል ኔት መሰረተ ልማት አጠቃቀምን የሚያሳይ ሪፖርት ሲያቀርቡ የቢሮው የአይ ሲቲ ባለሙያ አቶ ታዬ ወልደኪዳን በበኩላቸው በስኩል ኔት መሰረተ ልማት አጠቃቀምና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ግንዛቤ የሚፈጥር የመወያያ ሰነድ አቅርበው የውይይቱ ተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በተጨማሪ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በክፍለከተማው የፕላዝማ ትምህርት ተማሪዎች በአግባቡ እንዲማሩ የተከናወነ ተግባር እንደተሞክሮ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry