ቀን 24/5/2014 ዓ.ም

የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብር ተካሄደ።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በምርጥ ተሞክሮ ቀማሪ ቡድኑ አማካኝነት የአንዶዴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ያለውን ተሞክሮና ልምድ ለሌሎች አቻ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች አጋርቷል።

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለልኝ ወንዴ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ልምድ ልውውጦች በተቋማት መካከል ያለውን ክፍተት ከማቀራረብ ባለፈ በተማሪዎች ውጤት ላይም አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ገልፀዋል። በቀጣይም ቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ምርጥ ተሞክሮውን ለሌሎች አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የሚያጋራ መሆኑን አቶ አለልኝ ወንዴ አስታውቀዋል።

በመድረኩ የአንዶዴ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በምድረ ግቢ አያያዝ በመምህራን አቅም ግንባታና በተማሪዎችና በመምህራን መካከል የመወያያ መድረክ በመፍጠር መጠነ መድገምና ማቋረጥን መቀነስ መቻሉ እንዲሁም የተማሪዎች ፓርላማን በማጠናከር ዴሞክራሲን ባህል ለማድረግ የተሄደው ርቀት መልካም መሆኑ ተገልጿል።

ተሞክሮዎቹ በገለፃ መልክ ለተሳታፊዎች ከቀረቡ በኋላ ሁሉንም ስራዎች የመስክ ምልከታ በማካሄድ ተጎብኝተዋል።

በምርጥ ተሞክሮ ልምድ ልውውጡ ላይ የወረዳ 2 አስተዳደር አመራሮች የቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ር/መምህራን እና የወረዳዎች ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች መገኘታቸዉን ከከፍለ ከተማዉ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry