ቀን 19/5/2014 ዓ.ም

2014 ዓ.ም የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ የተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሄደ።

በመርሀ ግብሩ የልደታ ፣ የኮልፌ ቀራኒዮ እና የንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማዎች የ2014 ዓ.ም የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም በቢሮ እቅድ በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር በሆኑት በእቶ ጌታሁን ለማ ቀርባል።

በመርሀ ግብሩ በቀረቡት ሪፓርቶች ላይ ሰፊ ውይይት ከተካሄደ በሃላ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ማጠቃለያ እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን በእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መርሀ ግብሩ የክፍለከተማ እና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣ሱፐር ቫይዘሮች እና የትምህርት ባለሙያዎችን ጨምሮ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር እና የወላጅ ተማሪ ህብረት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry