ቀን 20/5/2014 ዓ.ም

“ኩረጃ በቃ!” ንቅናቄ ተጀመረ፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ ቤት በ2014 ዓ.ም የተማሪዎችን ስነምግባርና ውጤት ለማሻሻል ከጀመረው ስራ አንዱ የሆነውን “ኩረጃ በቃ!” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ የክፍለ ከተማው 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በተገኙበት በዛሬዉ እለት አስጀምሯል፡፡

የንቅናቄ መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሽታዬ መሃመድ ተማሪዎች ቀጣይ ሃገር ተረካቢ እንደመሆናችሁ ሃገራችሁ እናንተን ለማገዝ ሰፊ ስራዎች እየሰራች እንደሆነ በመገንዘብ በጥሩ ውጤትና ስነ-ምግባር ኩረጃን በመጠየፍ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ አሳስባለሁ ብለዋል ፤ በመድረኩ የተገኙ ተማሪዎችም ኩረጃን በማጥፋት አርአያነታቸውን እንዲያሳዩ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ በበኩላቸው የንቅናቄ መድረኩ መከፈት በ2014 ዓ.ም የታቀደው የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል ተግባር አንዱ ክፍል እንደሆነ ገልጸው፤ ተማሪዎች ከዚህ ንቅናቄ መድረክ በኋላ የስነምግባር ክፍተት ያለባቸውን ተማሪዎች የማረምና የማብቃት ከፍተኛ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተናግረዋል ፡፡

ትምህርት የተማሪዎችን እውቀት፤ክህሎትና አመለካት በማሳደግ ስብእናን ለማነጽ የሚያስችል የአንድ ሃገር ትልቅ መሳሪያ በመሆኑ እኩይ ስነምግባርና ኩረጃን መጠየፍ የተማሪዎች ልምድ እንዲሆን በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry