ቀን 20/4/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን በቅርቡ በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተመደቡ የአይ ሲ ቲ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው በዋናነት በስኩል ኔት መሰረት ልማት አጠቃቀም እና ተዛማጅ ጉዳዮችን በተመለከተ የተዘጋጀ ሲሆን ስልጠናውም በስራ ክፍሉ ባለሙያዎች በአቶ ታዬ ወልደኪዳን እና በአቶ ሚካኤል መስፍን ነው የተሰጠው።

በስልጠናው መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ እንዳስታወቁት ስልጠናው በቅርቡ ቢሮው ባወጣው ማስታወቂያ ተወዳድረው በየትምህርት ቤቱ የተመደቡ ባለሙያዎች ሙያዊ ክህሎታቸውን ማሻሻል እንዲችሉ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸው የስልጠናው ተሳታፊዎችም በትምህርት ቤቶች ያሉ የአይ ሲ ቲ መሰረተ ልማቶች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በቀረቡ የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን በዋናነትም የስራ ድርሻቸው በአስቸኳይ ለትምህርት ቤቶች ቢላክ የሚልና አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ተገቢውን ድጋፍ አለማድረጋቸውን አንስተው በቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ልማትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ በለጠ ንጉሴ እና በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪው በአቶ ደረጀ ዳኜ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry