ቀን 15/4/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት በመቀጠል በዛሬው እለት ከጤና አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር ተወያይቱዋል።

በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገራችን ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን የህግ ማስከበርም ሆነ የህልውና ዘመቻ በድል እንድታጠናቀቅ የጤና ሴክተሩ ከደጀንነት ጀምሮ ግንባር ድረስ እስከመዝመት የደረሰ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸው በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ የጤና ተቋማት ዳግም አገልግሎት እንዲጀምሩ 75 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ተወካይ አቶ ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ተገዳ ከገባችበት ጦርነት በፍጥነት ተላቃ ወደ መደበኛው የልማትና ብልጽግና ጎዳና እንድትመለስ የጤናው ሴክተር አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ውይይቱን ማካሄድ ማስፈለጉን ገልጸው ከአሸባሪው ቡድን ነጻ በወጡ አከባቢዎች የወደሙ ተቋማትን ወደስራ ለማስገባት የጤናው ሴክተር ያበረከተው አስተዋጾ ከፍተኛ መሆኑን እና በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም ሀገሪቱ ተገዳ የገባችበትን ጦርነት በድል እንድታጠናቅቅ ህይወታቸውን ከመገበር ጀምሮ የተለያዩ መስዋእትነቶችን ለከፈሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና መላው የጸጥታ መዋቅሮች ምስጋና አቅርበው በጦርነቱ የወደሙ የጤና ተቋማትን ዳግም ስራ ለማስጀመር በሚደረገው እንቅስቃሴ ሙያዊ ድጋፍ ከማድረግ ጀምሮ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

አካባቢያችንን #እንጠብቅ

ወደ ግንባር #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry