ቀን 8/4/2014 ዓ.ም

ፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ በስራ ላይ ባሉ የሕግ ማዕቀፎች ዙሪያ የንቃተ ህግ ትምህርት ተሰጠ፡፡

በጉለሌ ከፍለ ከተማ በኢየሩሳሌም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ በስራ ላይ ባሉ የሕግ ማዕቀፎች ዙሪያ ለህጻናቶች በሚመጥን መልኩ የንቃተህግ ትምህርት ተሰጠ።

የንቃተ ህግ ትምህርቱን ያዘጋጀው በፍትህ ሚኒስቴር የጉለሌ ከፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሲሆን ትምህርቱም በዐቃቢተ ህግ ምህረት በላይ አማካኝነት በተማሪዎች የሰልፍ ስነ-ስርዓት ላይ እንዲሰጥ የተደረገ ሲሆን መሰል ትምህርቶች ተማሪዎች ህግ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚኖራቸዉን ግንዛቤ ለማሳደግ እንደሚጠቅም ተመላክቷል።

አካባቢያችንን #እንጠብቅ

ወደ ግንባር #እንዝመት

መከላከያን #እንደግፍ

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry