ቀን 30/3/2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ቢሾፍቱ በሚገኘው የመከላከያ ኮንፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት በህልውና ትግሉ ጉዳት ለደረሰባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት የበጎች ስጦታ አበረከቱ ።

የበግ ስጦታውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ለሆስፒታሉ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተገኝ ለታ ያበረከቱ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላን ጨምሮ ተማሪዎች ፣መምህራን፣የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተው ጉዳት የደረሰባቸውን የመከላከያ ሰራዊት አባላት አበረታተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ድጋፉን ባበረከቱበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የትምህርት ማህበረስቦች በህልውና ማስከበር ትግሉ ጉዳት ለደረሰባቸው ጀግና የመከላከያ ሰራዊት አባላት 500 የሚጠጉና ግምታቸው ከ3.5ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ በጎችን ይዘው መገኘታቸውን ጠቁመው እነዚህ ጀግና የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የእናት ሀገራቸውን ሉአላዊነት ለማስከበር ለከፈሉት ታሪክ የማይረሳው መስዋእትነት ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል።

የሆስፒታሉ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተገኝ ለታ ድጋፉን ከተረከቡ በኋላ እንደገለጹት በህግ ማስከበርና በህልውና ዘመቻው ጉዳት ለደረሰባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት የትምህርት ማህበረሰቡ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው የሰራዊቱ ልፋትና መስዋእትነት በአሁኑ ወቅት እየተመዘገበ ባለው ድል ከንቱ እንዳልቀረ መረጋገጡንም አስገንዝበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry