ቀን 29/3/2014 ዓ.ም

ጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው እንጦጦ አምባ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለቢሮነትና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ባለ ሶስት ወለል ህንጻ ርክክብ ተካሄደ፡፡፡

ህንጻው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን የተገነባ መሆኑን እና ትምህርት ቤቱ ቀደም ብሎ ሲጠቀምበት የነበረው ህንጻ በመንገድ መስፋት ምክንያት ፈርሶ ቦታው ለተደራጁ ወጣቶች ሱቅነት እንዲውል በመደረጉ ምክንያት ህንጻው በመተኪያነት መገንባቱን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ መሀመድ ሀሰን ገልጸዋል፡፡

ርዕሰ መምህሩ አክለውም ህንጻው የርዕሰ መምህራንን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን ቢሮ ጨምሮ እንዲሁም የመምህራን ዲፓርትመንቶችን እንዲሁም የመሰብሰቢያ አዳራሽ ያካተተ መሆኑን ገልጸው ቀደም ብሎ በቢሮ እጥረት ምክንያት ለተለያዩ የቢሮ ስራዎች ሲያገለግሉ የነበሩ ክፍሎች ለመማር ማስተማር ስራው እንደሚውሉም ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፤ምክትል ቢሮ ኃላፊዎቹ አቶ አድማሱ ደቻሳ እና አቶ ሳምሶን መለሰን ጨምሮ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ኃላፊ አቶ ታከለ በትምህርት ቤቱ ተገኝተው የህንጻውን ግንባታ እንዲሁም ምን ያህል ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑን ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry