ቀን 29/3/2014 ዓ.ም

የግልና የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች የችግኝ እንክብካቤ አከናውነዋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የግልና የመንግስት ትምህርቶች ቤቶች ተማሪዎችና መምህራን፤ የትምህርት ጽ/ቤት ሰራተኞች እንዲሁም አመራሮች በችግኝ እንክብካቤው ላይ ተሳትፈዋል።

በዕለቱ የነበሩ ተሳታፊዎች በተለያዩ ሀገራት በሚነገሩ ቋንቋዎች #NOMORE! በማለት ድምጻቸውን ያሰሙ ሲሆን ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደንቦስኮ ትምርት ቤት መምህራንና ተማሪዎች ተናግረዋል።

በስፍራው ተገኝተው ለተሳታፊዎች መልዕክት ያስተላለፉት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ እንደተናገሩት ተማሪዎችና መምህራን አካባቢያቸውን በመጠበቅ፤ ችግኞችን በመንከባከብ፤ ለመከላከያ ሰራዊት በደም ልገሳና በስንቅ ዝግጅት በማገዝ የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ በመሆኑ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

አቶ አደፍርስ አክለውም በየትኛውም የልማት ስራና ሀገራዊ ጥሪ ላይ የትምህርት ተቋማት ግንባር ቀደም ሆነው በመሰለፍ ድርሻቸውን በመወጣት ላይ ናቸው ይህንንም አናጠክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry