ቀን 29/3/2014 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተከበረ፡፡

ወንድማማችነት ለህብረ-ብሄራዊ አንድነት! በሚል መሪ ቃል ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በድምቀት ተከበረ፡፡

የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በመስቀል የበአሉን ስነ-ስርአት ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በዓሉን በማስመልከት ባስተላለፉት መልእክት በአሉን ስናከብር ሃገራችን ያለችበትን ሁኔታ በማስተዋልና አሸባሪው ቡድን በወረራቸው ቦታዎች የተፈፀሙ ግፎችን በማውገዝ ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ሃገራችን ላይ የተፈጠረውን ችግር ለማክሸፍ ጫና በመፍጠርና በመደጋገፍ በተሰማራንበት ግንባር ሃላፊነታችንን እንወጣ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በዓሉ ኢትዮጵያ ብዝሀነት ያለባት ሃገር መሆኗን እውቅና ከመስጠት ባለፈ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በልዩነት ውስጥ ያለ አንድነታቸውን የማይፈታተንና ባህልና ቋንቋችንን የምናሳድግበት መድረክ ነው ያሉት የትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ ሃገራችን ህልውናዋ የሚፈተንበት ጊዜ ላይ ብንሆንም የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦችን አንድነት ለውስጥም ለውጪም ጠላቶች የምናሳውቅበት ልዩ ቀን መሆኑ በአሉን ከሌላው ጊዜ ለየት ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በወቅቱ የመወያያ ሰነድ ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በመጡ ባለሙያ አቶ ማናየ አባይ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል የበአሉ ተሳታፊዎችም በአሉን ከማክበር ባለፈ ወቅቱ አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው ብለዋል፡፡

በአሉን በማስመልክት የጽዳት ስራዎችም በቢሮ አመራሮች እና በሰራተኞች ተከናውነዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry