ቀን 29/3/2014 ዓ.ም

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የጀሞ 1 ትምህርት ጽ/ቤት ውስጥ የሚገኘው ስኩሎፍ ሪደምሽን ትምህርት ቤት “ወንድማማችነት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል 16ኛውን የኢትዮጲያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በድምቀት አከበረ።

በስነ ስርዓቱ የተለያዩ አስተማሪ የሆኑ ድራማዎችን እና የፈጠራ ስራዎችን ተማሪዎች ያቀረቡ ሲሆን በተለይ ደግሞ ማየት ለተሳናቸው የተሠራ ዘንግ ለይታ ለታዳሚዎች አቅርበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ እንደተናገሩት የዘንድሮውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ልዩ የሚያደርገው በኢትዮጲያ ብሄር ብሄረሰቦች ላይ የተከፈተብንን የህልውና አደጋ አንድ ሁነን እየመከትን ባለንበት ወቅት መሆኑ ነው ብለው ኢትዮጲያ ለባርካታ ጊዜያት ችግር ገጥሟታል የገጠሟትን ችግሮች ግን ህዝቦቿ አንድ ሆነው በመቆማቸው በድል ተወጥተውታል ሲሉ ሃሳባቸውን ገልፀዋል።

የክብረ በዓሉ ተሳታፊ ተማሪዎች እንዳሉት አባቶቻችን በኢትዮጲያ የማይደራደሩ ነበሩ፤ አሁንም ኢትዮጲያ በሷ የማይደራደሩ ልጆች አሏት ብለው የአባቶቻችንን አኩሪ ታሪክ በመድገም የኢትዮጲያን ነፃነት አስጠብቀን ለመሄድ ቃል ኪዳናችንን ማደስ ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry