ቀን 24/3/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ጋር በመተባበር በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ የመምህራን ማህበር ሰብሳቢዎች በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንዳስታወቁት ሀገራችን እያደረገችው ያለው የህልውና ትግል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከመጣ ሀይል ጋር መሆኑን በመገንዘብ የትምህርት ማህበረሰቡ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ደጀንነቱን በማረጋገጥ ላይ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

ኃላፊው አክለውም በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ እያካሄደችው ያለውን ፍትሀዊ ጦርነት አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሱ ሀሰተኛ መረጃዎችን ከመታገል አንጻር መምህራን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸው የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስም መምህራን ተሳትፎአቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቅአለም ቶሎሳ በበኩላቸው ሀገራችን የተቃጣባትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ በምታደርገው ተጋድሎ የሙያ ማህበሩ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው መምህራን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አግባቦችም ሆነ በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችን መታገል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry