ቀን 24/3/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ኢንጄንደር ሄልዝ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የነጭ ሪባን ቀንን ገላን የወንዶች አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አከበረ።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ዘውዴ እንዳስታወቁት የነጭ ሪባን ቀን ዘንድሮ “ሰላም ይስፈን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት አሁን ይቁም” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ገልጸው በትምህርት ቤቶችም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጭ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃትን መከላከል የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኢንጄንደር ሄልዝ ዳይሬክተሯ መስከረም ደምሴ በበኩላቸው ድርጅታቸው ትኩረት አድርጎ ከሚሰራባቸው ጉዳዮች መካከል በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን መከላከል የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን መሆኑን ጠቁመው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በትምህርት ቤቶች የሚስተዋሉ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመቅረፍ ድርጅታቸው በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ባለሙያዋ ወይዘሮ ትግስት በሪሁን የነጭ ሪባን ቀን በዋናነት ወንዶች ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ታስቦ የሚከበር በመሆኑ ቀኑን ገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲከበር መደረጉን ጠቅሰው ፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የበኩላቸውን ኃላፊነት ለተወጡት ኢንጄንደር ሄልዝ እና ለገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤት ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩ እለቱን የተመለከቱ የተለያዩ የስነ ጽሁፍ ስራዎች በተማሪዎችና መምህራን ከመቅረቡ ባሻገር ቀኑን በተመለከት ፓናል ዲስከሽን ተካሂዷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry