ቀን 23/3/2014 ዓ.ም

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 20 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል ገቡ፡፡

200 የሚደርሱ የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ እስከ 20 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል ገቡ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ(ዶ/ር) ተቋማቱ ላደረጉት ድጋፍ አመስግነው አገር ለማፍረስ የተነሳውን የጥፋት ኃይል ባጭር ጊዜ በማጥፋት ህብረብሄራዊ አንድነቷ የተጠናከረ ኢትዮጵያን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ትምህርት ላይ በመስራት አገሩንና ህዝቡን የሚወድ ዜጋ ማፍራት እንደሚገባም ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር ፕሬዚዳንት ሞላ ጸጋዬ( ዶ/ር) የትምህርት ተቋማቱ ገንዘቡን እስከ መጪው አርብ ድረስ ገቢ እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማህበር አባላትም በህልውና ዘመቻው የዘማች ልጆችን በማስተማርና በሌሎችም ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ገልጸው አስፈላጊ ከሆነም እስከ ግንባር ለመዝመት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry