ቀን 22/3/2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤቶች ስላለው የመማር ማስተማር ሂደትና በቀጣይ ሲለሚከናወኑ ተግባራት ከክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ውይይቱ በዋናነት ወቅታዊው የሀገሪቱን ሁኔታ መሰረት በማድረግ በየትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ስራው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲቀጥል እና ይህንኑ ተግባር እንዲደግፉ በየደረጃው የተቋቋሙ የኮማንድ ፖስት አደረጃጀቶች ኃላፊነታቸውን በምን መልኩ እየተወጡ እንደሚገኙ ለማወቅ የተካሄደ ግምገማ ነው፡፡

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንዳስታወቁት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ተግባሩ ያለምንም የጸጥታም ሆነ ሌላ ችግር ሳይስተጉዋጎል መቀጠል እንዲችል ከጸጥታ አካላትም ሆነ ከሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር መስራት ተገቢ መሆኑን ገልጸው የትምህርት ሴክተሩ ሀገሪቱ ለገባችበት የህልውና ዘመቻ ደጀንነቱን ለማሳየት በጥቂት ቀናት ውስጥ ተማሪዎችንና መምህራንን ያሳተፈ የንቅናቄ ፕሮግራም እንደሚካሄድም አስረድተዋል፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው ሀገሪቱ ተገዳ ወደ ህልውና ትግሉ ከገባች ጀምሮ በትምህርት ሴክተሩ የተለያዩ የደጀንነት ተግባራት ሲካናወኑ መቆየታቸውን ጠቁመው በቀጣይ ጊዜያትም እነዚህኑ ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲቻል ደም የመለገስና የዘማች ቤተሰቦችን የመደገፍ እንዲሁም ተማሪዎች በስንቅ ዝግጅት የበኩላቸውን አሻራ እንዲያኖሩ ለማስቻል እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry