ቀን 21/3/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ለሚካሄድ ሱፐር ቪዥን በተዘጋጀ ቼክ ሊስት ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ የክፍለ ከተማና ክላስተር ሱፐር ቫይዘሮች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ሱፐር ቫይዘሮቹ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት በየተመደቡበት ትምህርት ቤት በመሄድ ተገቢውን መረጃ በመሰብሰብ ሪፖርት ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በውይይቱ እንደገለጹት ሱፐር ቪዥኑ በዋናነት ሀገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ሱፐር ቪዥን የሚመጡ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ የማጠቃለያ ውይይት እንደሚደረግና ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰሩ አስረድተዋል።

የቢሮው የትምህርት ቤት መሻሻልና ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ አብይ ተፈራ በቼክ ሊስቱ የተቀመጡ መጠይቆችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ሱፐር ቩዥኑ በየትምህርት ቤቱ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት መፍጠር እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን እና ተመሳሳይ ሱፐር ቪዥን በቢሮና ክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

ሠራዊቱን ይደግፉ!

ከደጀን እስከ ግንባር ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጎን ነን!

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry