ቀን 16/3/2014 ዓ.ም

ከትምህርት ማህበረሰቡ አካላት የተሰባሰቡ ድጋፎች ለተፈናቃይ ወገኖች እንዲደርሱ ተደረገ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከትምህርት ማህበረሰቡ አካላት ያሰባሰባቸዉን 50 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የምግብ አይነቶችን ፣ አልባሳቶችን ፣ የመማሪያ ቁሳቁሶችን እና የንጽህና መጠበቂያዎችን ደብረ ብርሀን ከተማ በመገኘት ለተፈናቃይ ወገኖች በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ጥረቱ በየነ አስረክበዋል።

አቶ ጥረቱ በየነ በመልዕክታቸዉ እንደገለጹት ከከተማ አስተዳደሩ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረዉ የሚቀጥሉ መሆኑን በመጥቀስ ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን ለማሳየት ድጋፍ መደረጉን በቀጣይም ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያ ቦታቸዉ ሲመለሱ እንዲቋቋሙ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዝዎን ምክትል አስተዳደር አቶ ሲሳይ ወ/አማኑኤል በበኩላቸዉ ድጋፉ የትምህርት ማህበረሰቡ ለተፈናቃይ ወገኖቹ አጋርነቱን ያሳየበት ነዉ በማለት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ምክትል አስተዳደሩ አያይዘዉም የተደረገዉ ድጋፍ ለተፈናቃዮች በፍትሃዊነት ተደራሽ እንደሚደረግ በመግለጽ አሸባሪዉ ቡድን የከፈተዉ የሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳን ለመመከት ሰፊ ተደራሽነት ያለዉ የትምህርት ማህበረሰቡ ትክክለኛ መረጃን ለህዝቡ እንዲያደርስ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ አደራ ብለዋል፡፡

በድጋፍ መርሃ ግብር የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ አቶ ደስታ አዳርጌ ፣ የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስተዳደር ትምርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛዉ ገብሩ ፣ የቢሮዉ ጽ/ቤት ሀላፊ እና የቢሮ ሀላፊ ቴክኒካል አማካሪ ፣የ7 ከፍለ ከተማዎች ት/ጽ ቤት ሀላፊዎች ፣ የከተማዉ የመምህራን ማህበር አባላት እና ርዕሳነ መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Like
Like Love Haha Wow Sad Angry